ለሰው ጠላቱ ይወጣል ከቤቱአማርኛ ምሳሌ ነው።

ትርጉሙ ለማስተካከል

ነቢይ በአገሩ አይከበርም ከሚለው አባባል ጋር ይሄዳል። ሰወች በአካባቢያቸው ማንነታቸው ስለሚታወቅ ገናና የመሆን እድላቸው አነስተኛ ነው። በማይታወቁበት አገር ግን ጥፋታቸውና አስተዳደጋቸው ስለማይታወቅ የመግነንና ያልሆኑቱን የመሆን የደጋፊወችም መብዛት ይገጥማቸዋል።